









|
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን!
በዓብይ ኃይል ወሥልጣን!
ዐሠሮ ለሰይጣን!
አግዐዞ ለአዳም!
ሰላም !
እምይእዜሰ!
ኮነ ! ፍስሐ ወሰላም! |
|
ትንሣኤ
“ሞተ በፈቃዱ ወተቀብረ በሥምረቱ” ሃይ.አበ ዘአትና.እንዲል በፈቃዱ ሞቶ ተቀብሮ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር አድሮ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በስልጣኑ ሞትንና መቃብርን ድል ነስቶ በዘመነ ማርቆስ እሁድ በመንፈቀ ሌሊት ተነስቶአል “ወተንሣእኩ በሥልጣነ ባሕቲትትየ” እንዳለ ቅ. ቄርሎስ. ትንሣኤውን በ3 ቀን ያደረገው በ2 ወይ በ4 ቀን ያላደረገው ይተነገረለት ትንቢትና ምሳሌ ይፈጸም ዘንድ ሲሆን ትንቢቱና ምሳሌውም ነቢዩ ዮናስ 3 መዓልትና 3 ሌሊት በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ማደሩ ነው.ማቴ12፣40 ምሳሌው ሲብራራ አሳ አንበሪ ይከርሰ መቃብር ዮናስ የጌታ ምሳሌ ሲሆን ትንቢቱን ባወቀ አናገረ ምሳሌውንም ባወቀ አስመሰለ ፍፃሜው ግን ኃጢአትን በምድር፣መርገምን በመስቀል፣ሞትን በሲኦል፣ጥፋትንም በመቃብር ማጥፋቱን ለማጠየቅ ነው.”አስተኅፈረ ኃጢአተ በዲበ ምድር ወሰዓረ መርገመ በዲበ ዕፀ መስቀል ወአብጠለ ሞተ በውስተ ሲኦል ወነሰተ ሙስና በውስተ መቃብር” እንዲል ሃይ.አበ መድኃኒታችን በአካለ ብርሃን ሲነሳ የመቃብር ጠባቂዎች ወደቁ መላዕክት ክእግሩ እንደ ሻሽ ተነጥፈው አመሰገኑ መቃብሩ ሳይከፈትም ወጣ ድል አድራጊው ጌታ ሞትና ሲኦልን ድል ነሳቸው.ዮሐ-20-11 አይሁድን ፈርተው ተሸሽገው የነበሩት ሐዋርያትም የመጀመሪያው ትንሳኤው መበስርት ለመሆን በታደለችው በመግደላዊት ማርያም አመልካችነት ወደ መቃብሩ ሲሄዱ”ስለምን ሕያውን ከመቃብር መካከል ትፈልጉታላቹ እንደተናገረ ተነስቶአል እንጂ በዚህ የለም” ዮሐ.20-1 የሚል ብሥራት ተቀበሉ. እንግዲህ ከላይ ከብዙ በጥቂቱ እንዳየነው ትንሳኤው ይህንን ሲመስል ይህ የበዓላት ሁሉ ቁንጮ ከሚባለው በዓለ ፋሲካ ጀምሮ እስከ በዓለ ዕርገት ድረስ ያለው ጊዜ ሁሉ ዘመነ ትንሳኤ ይባላል.በነዚህ ዕለታት በቤተ ክርስቲያን የሚሰበኩት ትምህርቶችና የሚዘመሩት መዝሙራት ሁሉ ይህንኑ በዓል ማዕከል ያደረጉ ናቸው.ይህንኑ ተከትሎ በትንሣኤው ሳምንት “ዳግማይ ትንሣኤ”የሚከበር ሲሆን በዚህ ዕለትም በቤተ ክርስቲያን የሚደርሰው ሥርዓት ከዋናው የትንሳኤ በዓል ጋር ፍጹም አንድ ነው. ከትንሳኤ ማግስት ጀምሮ ላሉት ቀናት የየራሳቸው ስያሜ ያላቸው ሲሆን በዚሁ መሰረት= ሰኞ = ማዕዶት(አብርሃም) ማክሰኞ = መላዕክት ረቡዕ = አልዓዛር ኅሙስ = አዳም ዓርብ = ፀ ኣተ ነፍስ ቅዳሜ = አንስት እሁድ=(ፈጸምነ፣ቶማስ)*ዳግማይትንሳኤ*ይባላሉ. የነዚህ ዕለታት ስያሜም መድኃኒታችን የፈጸመውን የድኅነት ስራ በዋናነት የሚያስታውሱን ሲሆኑ በተጨማሪም የሕይወት ትንሳኤ ባለተስፋ የሆኑትን ቅዱሳንን በማዘከር የማያልቀው ቸርነቱን እንድንገነዘብ ትምህርት የሚሰጡን ናቸው. በተለይም *ዳግማይ ትንሳኤ* ደግሞ ሐዋርያው ቶማስን “ርኢከኒሁ አመንከኒ”ያመንክ እንጂ ያላመንክ አትሁን ብሎ የተቸነከረውን ችንካርና የተወጋው ጎኑን አሳይቶ ያሳመነበት ቀን ነው.በአጠቃላይ እርሱ በኩረ ትንሳኤ ሆኖ ትንሳኤውን እንዳሳየን እኛም ሞተን የማንቀር የትንሳኤው ባለተስፋ መሆናችንንም የምናስብበት ዓቢይ ቀን መሆኑን ማስተዋል ይገባናል. ስለዚህ ሕዝበ ክርስቲያን ይህችን የደስታ በዓል በቤተ ክርስቲያን ማክበርና ፋሲካችንም እውንተኛው አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን መመስከር ያስፈልጋል.ዛሬ ዓለም ሁሉ ከሃይማኖት ርቆ በጊዜያዊና በማይጠቅም ነገር ራሱን እየደለለ በሞትና በጨለማ በሚመላለስበት በዚህ ዘመን የክብር ትንሳኤ ተስፈኞች በመሆን በበጉ ደም ልብሳቸውን አጥበው በቀኙ ከሚቆሙት ቅዱሳን ጋር ለመቆጠር መንፈሳዊ ተጋድሎ ማድረግ የጠበቅብናል. ማቴ 25- 34 ፣ራዕ 7- 14 አለዚያ ግን ዘመን እየቆጠሩ በዓል ብቻ መቁጠሩ የነፍስ ዋጋ አይሆነንም ከክርስትና ሕይወትም አንፃር በቂ ነው ሊባል የሚበቃ አይደለም. ይልቅስ ዘምኑን ዋጁት በተባለው መሰረት ራስን ለንስሃና ለስጋወደሙ ማዘጋጀት ትልቅ ሃላፊነት ነው.ለዚህም እግዚአብሔር አምላክ ኃይሉን ያድልን.በዓሉን በዓለ ሰላም በዓለ ፍስሃ ያድርግልን. አሜን. (ምንጭ መዝገበ ታሪክ-ከመምህር ኅሩይ ኤርምያስ)
ሰባት ዋና ዋና ኃጢአቶችደ ኩራት...ሆዳምነት.......ንፍገት...........ሥጋዊእርካታ.......ስንፍና............ቅናት.......ቁጣ.... እነዚህ ሰባት ኃጢአቶች ለእኛ ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ አደገኞችና ወደ መንፈሳዊና ዘለዓለማዊ ሞት ይመራሉ አንድ ሰው ንስሐ እስካልገባ ድረስ ኃጢያቶች ሁሉ አደገኞች በመሆናቸው ወደመንፈሳዊና ዘለዓለማዊ ሞት ይመራሉ። ቅዱስ ጳውሎስ” የኃጢያት ደመወዝ ሞት ነው።” ( ሮሜ 6፤23 እና 5፡12) ብሏል። ተጨማሪ ያንብቡ
|