ምዕራፍ ፩      

        የሰማይና የምድር ፍጥረት

              (ዘፍጥረት ፩፥፩)

 

፩፣ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ። (ዘፍጥረት ፩፥፩)

የምንኖረባት ምድር ለዓይን የሚያምሩ፥ ለሕይወትም በሚጠቅሙ ነገሮች እንዴት ተሞላች! በላያችን ያለው ሰማይ በስፋቱ ያስግርማል፤ በየዕለቱም በፀሐይ ጮራ፥ ደመናዎች በሚያወዱልንም ዝናም እየተጠቀምን መልካም የሆነውን አየርን እየተነፈስን እንኖራለን። ምድሪቱም ለሰውነታችን የሚስማማውን እህል በየአመቱ ታበቅልልናለች። እኛም ባልፈጠርናቸው በስንትና በስንት ዓይነት ነገር ለልብስም ሆነ ለቤት፥ ለሥራ መሣሪያዎችም በሆኑ ነገሮች እየተጠቀምን እንኖራለን። በምንደክምበት ጊዜ ለእንቅልፍ የሚመቸው ጨለማ ማታ ማታ ይመጣልናል። ይህንም ሁሉ ስናስብ መኖርያ የሆነችልን ምድር በእውነት መልካም መኖርያ እንደ ሆነች እናስተውላለን።

  በመጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ የሚገኘው ቃል፥ ይህን ድንቅ መኖሪያ ያዘጋጀልን እግዚአብሔር እንድ ሆነ ይነግረናል። እግዚአብሔርም ሁሉን ቻይ ነውና ሰማይና ምድርን የፈጠረ በቃሉ ነው። የሰው ቃል አንዲህ ያለ ኃይል የለውም፤ እግዚአብሔር ግን በቃሉ ሲናገር፥ ያልሆኑትንም እንድ ሆኑት ሲጠራቸው ይፈጠራሉ ይሆናሉም። እንደ እግዚአብሔር አምላካችን ያለ አንድም የለም፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም። ሰማይና ምድር ሳይፈጠሩ፥ ዓመታትና ዘመናትም ሳይጀምሩ እግዚአብሔር ነበረ። እርሱም መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚኖር አምላክ ነው። 
          αααααααααα & ΩΩΩΩΩΩΩΩΩΩ

 

 

Back

ለልጆች