አርኪቭ

 

Torsdag 23. november  2006

ጥምቀተ እግዚእ ኢየሱስ ልደተ እግዚእ ኢየሱስ
Text Box: 					ትንሣኤ

“

			ሞተ በፈቃዱ ወተቀብረ በሥምረቱ” ሃይ.አበ ዘአትና.እንዲል በፈቃዱ ሞቶ ተቀብሮ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በመቃብር አድሮ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በስልጣኑ ሞትንና መቃብርን ድል ነስቶ በዘመነ ማርቆስ እሁድ በመንፈቀ ሌሊት ተነስቶአል “ወተንሣእኩ በሥልጣነ ባሕቲትትየ” እንዳለ ቅ. ቄርሎስ.
   ትንሣኤውን በ3 ቀን ያደረገው በ2 ወይ በ4 ቀን ያላደረገው ይተነገረለት ትንቢትና ምሳሌ ይፈጸም ዘንድ ሲሆን ትንቢቱና ምሳሌውም ነቢዩ ዮናስ 3 መዓልትና 3 ሌሊት በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ማደሩ ነው.ማቴ12፣40 ምሳሌው ሲብራራ አሳ አንበሪ ይከርሰ መቃብር ዮናስ የጌታ ምሳሌ ሲሆን ትንቢቱን ባወቀ አናገረ ምሳሌውንም ባወቀ አስመሰለ ፍፃሜው ግን ኃጢአትን በምድር፣መርገምን በመስቀል፣ሞትን በሲኦል፣ጥፋትንም በመቃብር ማጥፋቱን ለማጠየቅ ነው.”አስተኅፈረ ኃጢአተ በዲበ ምድር ወሰዓረ መርገመ በዲበ ዕፀ መስቀል ወአብጠለ ሞተ በውስተ ሲኦል ወነሰተ ሙስና በውስተ መቃብር” እንዲል ሃይ.አበ
   መድኃኒታችን በአካለ ብርሃን ሲነሳ የመቃብር ጠባቂዎች ወደቁ መላዕክት ክእግሩ እንደ ሻሽ ተነጥፈው አመሰገኑ መቃብሩ ሳይከፈትም ወጣ ድል አድራጊው ጌታ ሞትና ሲኦልን ድል ነሳቸው.ዮሐ-20-11 አይሁድን ፈርተው ተሸሽገው የነበሩት ሐዋርያትም የመጀመሪያው ትንሳኤው መበስርት ለመሆን በታደለችው በመግደላዊት ማርያም አመልካችነት ወደ መቃብሩ ሲሄዱ”ስለምን ሕያውን ከመቃብር መካከል ትፈልጉታላቹ እንደተናገረ ተነስቶአል እንጂ በዚህ የለም” ዮሐ.20-1 የሚል ብሥራት ተቀበሉ. 
 እንግዲህ ከላይ ከብዙ በጥቂቱ እንዳየነው ትንሳኤው ይህንን ሲመስል ይህ የበዓላት ሁሉ ቁንጮ ከሚባለው በዓለ ፋሲካ ጀምሮ እስከ በዓለ ዕርገት ድረስ ያለው ጊዜ ሁሉ ዘመነ ትንሳኤ ይባላል.በነዚህ ዕለታት በቤተ ክርስቲያን የሚሰበኩት ትምህርቶችና የሚዘመሩት መዝሙራት ሁሉ ይህንኑ በዓል ማዕከል ያደረጉ ናቸው.ይህንኑ ተከትሎ በትንሣኤው ሳምንት “ዳግማይ ትንሣኤ”የሚከበር ሲሆን በዚህ ዕለትም በቤተ ክርስቲያን የሚደርሰው ሥርዓት ከዋናው የትንሳኤ በዓል ጋር ፍጹም አንድ ነው.
  ከትንሳኤ ማግስት ጀምሮ ላሉት ቀናት የየራሳቸው ስያሜ ያላቸው  ሲሆን በዚሁ መሰረት=
            ሰኞ     = ማዕዶት(አብርሃም)
            ማክሰኞ = መላዕክት
            ረቡዕ    = አልዓዛር
            ኅሙስ   = አዳም
            ዓርብ    = ፀ ኣተ ነፍስ
            ቅዳሜ   = አንስት 
            እሁድ=(ፈጸምነ፣ቶማስ)*ዳግማይትንሳኤ*ይባላሉ.                                                             የነዚህ ዕለታት ስያሜም መድኃኒታችን የፈጸመውን የድኅነት ስራ በዋናነት የሚያስታውሱን ሲሆኑ በተጨማሪም የሕይወት ትንሳኤ ባለተስፋ የሆኑትን ቅዱሳንን በማዘከር የማያልቀው ቸርነቱን እንድንገነዘብ ትምህርት የሚሰጡን ናቸው. በተለይም *ዳግማይ ትንሳኤ* ደግሞ ሐዋርያው ቶማስን “ርኢከኒሁ አመንከኒ”ያመንክ እንጂ ያላመንክ አትሁን ብሎ የተቸነከረውን ችንካርና የተወጋው ጎኑን አሳይቶ ያሳመነበት ቀን ነው.በአጠቃላይ እርሱ በኩረ ትንሳኤ ሆኖ ትንሳኤውን እንዳሳየን እኛም ሞተን የማንቀር የትንሳኤው ባለተስፋ መሆናችንንም የምናስብበት ዓቢይ ቀን መሆኑን ማስተዋል ይገባናል. 
  ስለዚህ ሕዝበ ክርስቲያን ይህችን የደስታ በዓል በቤተ ክርስቲያን ማክበርና ፋሲካችንም እውንተኛው አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን መመስከር ያስፈልጋል.ዛሬ ዓለም ሁሉ ከሃይማኖት ርቆ በጊዜያዊና በማይጠቅም ነገር ራሱን እየደለለ በሞትና በጨለማ በሚመላለስበት በዚህ ዘመን የክብር ትንሳኤ ተስፈኞች በመሆን በበጉ ደም ልብሳቸውን አጥበው በቀኙ ከሚቆሙት ቅዱሳን ጋር ለመቆጠር መንፈሳዊ ተጋድሎ ማድረግ የጠበቅብናል. ማቴ 25- 34 ፣ራዕ 7- 14 አለዚያ ግን ዘመን እየቆጠሩ በዓል ብቻ መቁጠሩ የነፍስ ዋጋ አይሆነንም ከክርስትና ሕይወትም አንፃር በቂ ነው ሊባል የሚበቃ አይደለም. ይልቅስ ዘምኑን ዋጁት በተባለው መሰረት ራስን ለንስሃና ለስጋወደሙ ማዘጋጀት ትልቅ ሃላፊነት ነው.ለዚህም እግዚአብሔር አምላክ ኃይሉን ያድልን.በዓሉን በዓለ ሰላም በዓለ ፍስሃ ያድርግልን. አሜን. 
(ምንጭ መዝገበ ታሪክ-ከመምህር ኅሩይ ኤርምያስ)

-

 

ምልክት ነው።

 

ቤተክርስቲያን ሁሉንም ያለ ምሳሌና ያለ ትርጉም የምትፈጽመው የላትም ። እኛም ስለበዓሉ

ትርጓሜ ካወቅን ጌታ በተናቀችው አህያ ከብሮ እንደዋለ በዚህ ዓለም አልባሌና ተርታ መስለው

ለፈጣሪያቸው በትህትና በመገዛት ከሰብአው ዓለም በጾም በጸሎት በትሩፋት ተለይተው ዓለም

እንደ ኋላ ቀርና እንደ አላዋቂ የቆጠረቻቸውን ክርስቲያኖች ላይ ጌታ ከብሮ ገኖ ለመታየቱ ምሳሌ

ስለሆነ እንደ አህያይቱ በልቦናችን ዙፋን ላይ ነግሶ እንዲኖር ልባችንን ክፍት እናድርግ!!

        በዓሉን በዓለ ጥዒና ያድርግልን ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

 

Text Box: 	
		
		

		

	
		
		”የታሰሩትን አህዮች ፈታችሁ አምጡልኝ!” ማቴ 21፡2 
	
	ሕዝበ ክርስቲያን እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና አደረሳችሁ!
	
	ሆሣዕና ማለት መድሃኒት ማለት ነው። በተብራራ ትርጉሙ ሲታይ ሆሣዕና ማለት ’አሁን አድን’ ማለት ሲሆን ’ሆሣዕና በአርያም ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት፤ ብሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር’ እያሉ በእለቱ ፈጣሪያቸውን በደስታ ዝማሬ እየዘለሉ ሲያመሰግኑ የነበሩትን የህፃናቱንና የአዕሩጋን ድምጽ የምናስብበት ዕለት ነው።
	ይህ በታላቁ አብይ ጾም መገባደጃ ላይ በስምንተኛው እሑድ የሚውለው ቀን ጌታ በትንቢት እንደተነገረለት በአህያይቱና በውርንጫዋ ለይ ተቀምጦ መላዋ ኢየሩሳሌም እስክትንቀጠቀጥ ድረስ በታላቅ ሞገስ ከብሮ ወደ ቤተ መቅደስ በዑደት የገባበት የክብረ በዓሉ ቀን ሲሆን በዕለቱ ’ማንም ቢጠይቃችሁ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉ’ ተብሎ በተነገረው መሰረት ተፈትተው ከመጡት አህዮች ጀምሮ እስከ ቤተ_መቅደስ ያደረገው ጉዞ ሁሉ ታላቅ መንፈሳዊ ምስጢራት የተፈፀሙበት መሆኑን ልናስተውለው ይገባል።
	ትርጓሜው 
1.ሁለቱ አህዮች የአዳምና የሔዋን ምሳሌ ሲሆን መታሰራቸው አዳምና ሔዋን ዕፀ በለስ በልተው በግብርናተአስረው  ዲያቢሎስ በሲኦል ቁራኛ ታስረው ለመኖራቸው ምሳሌ መፈታታቸው ጌታችን ሰው ሆኖ ደሙን አፍስሶ ነፃ ለማውጣቱ

2.ሁለቱ አህዮች የብሉይና የሐዲስ ምሳሌ ሲሆኑ በማቴ 21  ከቁጥር 1 እስከ ፍጻሜ እንደ ተጠቀሰው በአህያይቱ እስከ ቤተ መቅደስ በውርንጫዋ ደግሞ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ዑደት አድርጓል። ይህም ሕገ ኦሪት( ብሉይ) ስትመራን ኖራ በአዲሱ ህግ  (በሐዲስ ኪዳን) ለመተካቷ ምሳሌ ነው።

 3.የዘንባባ ዝንጣፊ _ቀደም ሲል በዘመነ ኖህ ርግብ ማየ አይህ ለመድረቁ የብስራት ምልክት አምጥታለች። በመጽሐፈ ዮዲትም እንደምንረዳው ዮዲት የአህዛብ ንጉስ ሆሊሆርኒስን ድል ነስታ ስትመጣ ህዝቡ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዞ በሆታ ተቀብሏታል። መጽ (ዮዲትን ተመልከት) ስለዚህ ማየ ኃጢያት ቁሞ ማየ ሕይወት እንደተሰጠን ግብርናተ ዲያቢሎስ ቀርቶልን ግብርናተ ሥላሴን መታተማችንን ለማብሰር ምልክት ሲሆን ዲያቢሎስ የመሸነፉ ጌታ ድል የማድረጉ የድል ምልክት ነው።

ቤተክርስቲያን ሁሉንም ያለ ምሳሌና ያለ ትርጉም የምትፈጽመው የላትም ። እኛም ስለበዓሉ
ትርጓሜ ካወቅን ጌታ በተናቀችው አህያ ከብሮ እንደዋለ በዚህ ዓለም አልባሌና ተርታ መስለው
ለፈጣሪያቸው በትህትና በመገዛት ከሰብአው ዓለም በጾም በጸሎት በትሩፋት ተለይተው ዓለም
እንደ ኋላ ቀርና እንደ አላዋቂ የቆጠረቻቸውን ክርስቲያኖች ላይ ጌታ ከብሮ ገኖ ለመታየቱ ምሳሌ
ስለሆነ እንደ አህያይቱ በልቦናችን ዙፋን ላይ ነግሶ እንዲኖር ልባችንን ክፍት እናድርግ!!
		በዓሉን በዓለ ጥዒና ያድርግልን ወስብሐት ለእግዚአብሔር። 
፡                   ሆሣዕና